Arts TVArts TV
← NewsPolitics

68ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በተለያዩ  ጉዳዮች ላይ ዉሳኔ አሳለፈ

Arts TV · ሜይ 20 2019

68ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በተለያዩ  ጉዳዮች ላይ ዉሳኔ አሳለፈ

68ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በተለያዩ  ጉዳዮች ላይ ዉሳኔ አሳለፈrnrnየሚኒስትሮች  ምክር ቤት  ባካሄደው 68ኛ  መደበኛ ስብስባ  በተለያየ ጉዳዩች ላይ የተወያየ ሲሆን ፤ ከዚህ በፊት   ወጥቶ በነበረው የፀረ ሽብርተኝነት  አዋጅ በይዘት እና በአፈፃፀም  ክፍተቶች የነበሩበት  በመሆኑ  ጠቅላይ አቃቤ ህግ  የሌሎች ሀገራትን አለም አቀፍ ነበራዊ ሁኔታ ያገነዘበ  አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚነስትሮች ምክር ቤት  ውሳኔ አቅርቧል፡፡rnrnምክርቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ  ላይ በዝርዝር  ከተወያየ በኃላ ማሻሻያዎችን  በመጨመር  ለህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡rnrnበሌላ በኩል የተጨማሪ እሴት ታክስ  አዋጅን ለማሻሻል ተዘጋጅቶ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአዋጁን አፈፃፀም  በአዲስ አዋጅ መተካት አስፈላጊ በመሆኑ  ፤ችግሩን ለመፍታት የገቢዎች ሚኒስቴር  እና የገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስን  አዋጅን ለማሻሻል  ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅተው  ለሚኒስትሮች ምክርቤት ውሰኔ አቅርበዋል፡፡rnrnምክርቤቱም በቀረበው  ረቂቅ አዋጅ ላይ  ከተወያየ በኃላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን  በመጨመር  ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንዲተላለፍ መወሰኑ ተነግሯል፡፡rnrnምክርቤቱ በቀረቡ ሶስት ከፍተኛ ደረጃ የመአድን   ማምረት  ስምምነት ፍቃዶች ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ  ስምምነቶቹ  በስራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡

More in Politics