ፕሮፌሰር ብርሃኑና አቶ አንዱአለም የኢዜማ መሪና ምክትል መሪ በመሆን ተመረጡrnrnፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዱአለም አራጌ የኢትዮጵያ ዜጎች ማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ መሪና ምክትል መሪ በመሆን ተመረጡ፡፡rnrnበዛሬው ዕለት በተካሄደው ምርጫ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 912 ድምፅ በማግኘት የፓርቲው መሪ በመሆን ተመርጠዋል፡፡rnrnበተመሳሳይ አቶ አንዱአለም አራጌ የፓርተዊው ምክትል መሪ በመሆን ተመርጠዋል፡፡rnrnእንደዚሁም አቶ የሸዋስ አሰፋ 722 ድምፅ በማግኘት ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፥ ዶክተር ጫኔ ከበደ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን ተመርጠዋል።rnrnኤፍቢሲ





