Arts TVArts TV
← NewsPolitics

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሀ ከስልጣን ይውረዱ የሚል ግፊት በዝቶባቸዋል፡፡

Arts TV · ሜይ 15 2019

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሀ ከስልጣን ይውረዱ የሚል ግፊት በዝቶባቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሀ ከስልጣን ይውረዱ የሚል ግፊት በዝቶባቸዋል፡፡rnrnየቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ እና የአሁኑ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጂ ዊሀ የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ከውድቀት  መታደግ አልቻሉም በሚል ተቃዋሚዎቻቸው ወይ ባአግባቡ ይምሩ ወይ ስልጣን ይልቀቁ እያሏቸው ነው፡፡rnrnፕሬዝዳንት ዊሀ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመመካከር እቅድ ቢኖራቸውም  ተቃዋሚዎቹ ግን በመጭው ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል ነው የተባለው፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ዊሃ ተቃዋሚዎቹ ለተቃውሞ ጎዳና ከመውጣታቸው በፊት ሀሳባቸውን ለውይይት ቢያቀርቡ መልካም ነው ይህን ማድረግ ካልፈለጉ ግን መብታቸው ነው ብለዋል፡፡rnrnዊሃ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የመጀመሪያው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን ተከትሎ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀገሪቱ አለመረጋጋት እንዳይከሰት ከወዲሁ ስጋታቸውን እየገለፁ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Politics