ፕሬዝዳንት አልበሽር ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡rnrnከወራት በፊት በህዝባዊ አመፅ ተገፍተው ከስልጣናቸው የወረዱት የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ፍርድ ቤት የቀረቡት ሀገራቸው ከሳቸው አገዛዝ በኋላ የሲቪል መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ስምምነት ባደረገች ማግስት ነው፡፡rnrnአልበሽር ክስ የተመሰረተባቸው በሙስና፣በርካታ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በቤታቸው እና በቢሯቸው በማከማቸት እንዲሁም ያልተገባ ስጦታ በመቀበል ወንጀል ነው ተብሏል፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው አቃቤ ህግ ህገ ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ በመጠቀም ወንጀል ጥርጥሯቸው ሌላ ምርመራ ከፍቶባቸዋል፡፡rnrnአልበሽር ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው ቀደም ብሎ አመንስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብዓዊ መብት ተቋም ፕሬዝዳንቱ ለፍርድ መቅረባቸው ጥሩ ሆኖ ሳለ አሁንም በሱዳን ህዝብ ላይ የፈፀሙት ወንጀል መጣራት አለበት የሚል አስተያየት መስጠቱ ይታወሳል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙrnrn





