ፍርድ ቤቱ ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ከ98 ቤቶች ውጪ ያሉት እንዳይተላለፉ የወጣው እግድ እንዲነሳ አዘዘrnrnየፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጦር ሀይሎች ምድብ ችሎት 8ኛ የፍትሃብሄር ችሎት እጣ ወጥቶባቸው የነበሩ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ ተጥሎ የነበረው እግድ ከ98 ቤቶች ውጪ ያሉት ቤቶች ላይ እግዱ እንዲነሳ አዘዘ።rnrnመጋቢት 26 ቀን 2011 ዓመተ መህረት 98 ፤100 በመቶ ክፍያ የፈፀሙ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ከሳሾች እጣ የወጣባቸው ቤቶች እንዳይተላለፉ የጠየቁትን አቤቱታን ችሎቱ ሲመረምር ቆይቷል።rnrnእጣ የወጣባቸው ከ18 ሺህ በላይ ቤቶች መሆናቸው የተመለከተው ፍርድ ቤቱ፥ በእነዚህ 98 ተከሳሾች ምክንያት ሌሎች ቤቶች ታግደው መቆየት የለባቸውም ሲል የሌሎችን ቤቶች እግድ አንስቷል።rnrnፍርድ ቤቱ 98 ቤቶች ማለትም 48 ባለ ሶሰት መኝታ፣ 43 ባለ ሁለት መኝታ እና ሰባት ባለ አንድ መኝታ ቤቶች ባሉበት ለማንም ሳይተላለፉ ታግደው እንዲቆዩ ፥ በቀሪዎቹ ቤቶች ላይ ግን እግዱ እንዲነሳ ሲል ትእዛዝ ሰጥቷል።rnrnበተጨማሪም ችሎቱ የፍትሃብሄር ህግ 41 መሰረት በእነ ዘላለም መዝገብ በሚል በአሁኑ እጣ የወጣላቸው ከ50 በላይ እድለኞች በሶስተኛ ወገን በመዝገቡ ላይ ጣልቃ እንግባ ብለው የጠየቁትን ጥያቄ ተቀብሎ ፈቅዷል።rnrnሌሎች 100 በመቶ ቆጥበናል ብለው የቀረቡ 130 ሰዎች ጥያቄን ውድቅ ያደረገው ፍርድ ቤቱ፥ በሌላ መዝገብ እንደ አዲስ ክስ መመስረት ትችላላቹ ብሏል።rnrnበሌላ በኩል 98 ቤቶች ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ ትእዛዝ የወጣላቸው 98 ከሳሾች ክሳቸውን አሻሽለው እና ለተከሳሽ ኪሳራ ከፍለው እንዲቀርቡ ለግንቦት 28 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።rnrnየጋራ መኖሪያ ቤቱን ለማግኘት ተመዝግበው 100 በመቶ የከፈሉ 98 ዜጎች ክስ መመስረታቸውን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የፍርድ ሂደቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ አግዶ የነበረው።rnrnተመዝጋቢዎቹም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒቴርን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝን እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ነው የከሰሱት።rnrnፋና እንደዘገበዉ በመመሪያው መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕጣ አውጥቶ ለእድለኞች ማከፋፈል ሲገባው የከተማ አስተዳደሩ መመሪያን በመጣስ 100 በመቶ የቆጠቡ ተመዝጋቢዎች እያሉ ከ40 በመቶ ጀምሮ የቆጠቡትን በእጣው በማካተት ዕጣውን በማውጣት ከሕግና ከውል ውጪ ቤቶቹ እጣ እንዳወጣባቸው በክሳቸው ላይ ጠቅሰዋል።
← NewsPolitics
ፍርድ ቤቱ ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ከ98 ቤቶች ውጪ ያሉት እንዳይተላለፉ የወጣው እግድ እንዲነሳ አዘዘ
Arts TV · ሜይ 27 2019





