ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ከዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ቦርዤ ብሬንዴ ጋር ከሲውዘርላንድ ዳቮስ የቀጠለ ውይይት አደረጉ።rnrnበጥር ወር 2011 እንደተወሰነው ኢትዮጵያ የ2013 የዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ በአፍሪካ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።rnrnበዛሬው እለት ጠ/ሚር አብይ ና ፕሬዝዳንት ቦርዤ ይህንኑ አሕጉራዊ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችንና አግባቦችን የሚያትት ስምምነት ተፈራርመዋል።rnrnየዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ በአፍሪካ በመስከረም ወር 2013 በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ከአንድ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል።rnrnምንጭ ፤-የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት
← NewsPolitics
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ከዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ቦርዤ ብሬንዴ ጋር ከሲውዘርላንድ ዳቮስ የቀጠለ ውይይት አደረጉ።
Arts TV · ሜይ 15 2019




