ግብፅ በቀይ ባህር የዓሳ ማጥመድ ስራ እንዳይካሄድ ከለከለለችrnrnየፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ መንግስት ይህን እርምጃ የወሰደው በአካባቢው ስነ ህይዎታዊ ሚዛንን ለመጠበቅ በማሰብ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡rnrnየዓሳ ሀብት ልማት ባለስልጣን መስሪያ ቤትን በሀላፊነት የሚመሩት ዶክተር አይመን አማር እንዳሉት በፈረንጆቹ ከየካቲት እስከ መስከረም ለሰባት ወራ ያህል በቀይ ባሀር አካባቢ ዓሳ ማስገር አይቻልም፡፡rnrnየግብፁ አክባር አል ዮም ጋዜጣ እንደዘገበው የሀገሪቱ መንግስት የወሰደው እርምጃ የውሀ ውስጥ ብዛሃ ህይዎት እንዳይጎዳ ያደርጋል፡፡rnrnበየዓመቱ ከቀይ ባህር የሚሰበሰበው 60 ሺህ ቶን የዓሣ ምርት የግብፅን የዓሣ ፍላጎት የሚያሟላው ሶስት በመቶውን ብቻ መሆኑን ባለ ስልጣናቱ ተናግረዋል፡፡rnrnበዚህም የተነሳ ግብፅ የዜጎቿን ከፍተኛ የዓሣ ፍላጎት ለማሟላት ስትለ በየዓመቱ ከውጭ ሀገር 300 ሺህ ቶን የዓሳ ምርት ታስገባለች፡፡rnrnባለፈው ዓመት በመንግስት ድጋፍ የተደረገለት ዓሰሣ እርባታ ዘርፍ ምርቱ አንዲጨምር ማድረጉ እጥረቱን ለመሸፈን እገዛ ማድረጉም ተመልክቷል፡፡rnrnአሁን የተወሰደው ዓሣ ማስገርን የሚከለክል እርምጃ የዓሣ ዋጋ እንዲጨም ያደርጋል የሚል ስጋት ቢፈጥርም ባለ ስልጣናቱ ግን ችግር እንደማይኖር ለህዝቡ ማረጋገጫ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡rnrnበመንገሻ አለሙ





