የግብፅ ፍርድ ቤት የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ከእስር እዲለቀቅ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡rnrnከ2 ዓመታት በላይ በግብፅ እስር ቤት ያሳለፈው የአልጀዚራው ጋዜጠኛ ሞሀመድ ሁሴን እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ ቢወስንም አቃቤ ህግ ፍርዱ ትክክል አይደለም ብሎ ይግባኝ አቅርቧል፡፡rnrnየጋዜጠኛው ጠበቃ ጣሂር አቡል ናስር ደንበኛቸው በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡rnrnዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው ጋዜጠኛው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2016 መደበኛ ክስ ሳይመሰረትበት ነው ወደ እስር ቤት የገባው፡፡rnrnመቀመጫውን ኳታር ዶሀ ያደረገው አልጀዚራ "ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም" የሚል መሪ ሀሳብ ይዞ የጋዜጠኛ ሁሴንን መታሰር በመቃወም በተደጋጋሚ ግብፅን ሲወቅስ ነበር፡፡rnrnግብፅ ሁሴንን ያሰረችው የሀሰት ዜና በማሰራጨት እና ለብጥብጥ የሚያነሳሳ ዘገባ ሲያስተላልፍ አግኝቸዋለሁ ብላ ነው፡፡rnrnየግብፅ መንግስት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2017 የትኛውም የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ እነዳይዘግብ እገዳ መጣሉ ይታወሳል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ




