Arts TVArts TV
← NewsAfrica

የዚምባቡየ ፍርድ ቤት መንግስት የዘጋውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲከፍት ትእዛዝ ሰጠ

Arts TV · ጃን 22 2019

የዚምባቡየ ፍርድ ቤት መንግስት የዘጋውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲከፍት ትእዛዝ ሰጠrnrnበዚምባቡየ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡን ተከትሎ በሀገሪቱ በተቀሰቀሰው አመፅ ስጋት የገባው የፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አስተዳደር የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉ በሀራሬ ሌላ ቁጣን አስነስቷል፡፡rnrnዘ ጋርዲያን እንደዘገበው በዚምባቡየ የኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠ ሳምንት አስቆጥሯል፡፡rnrnበዚህም ምክንያት ተቃውሞው እየበረታ ሄዶ በሰልፈኞቹ እና በፖሊስ በካከል በተፈጠረ ግጭት 12 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡rnrnየዚምባቡየ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢንተርኔት  መዘጋቱ አንድም ብጥብጡን ያባብሰዋል በሌላ በኩል ደግሞ መረጃ የማግኘት መብትን ይጋፋል በሚል መንግስት በአስቸኳይ አገልግሎቱን እንዲጀምር ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡rnrnየዚምባቡየ ንግድ ማህበር ዋና ፀሀፊ ጃት ሞዮን ለአባሎቻቸው ከቤት ያለመውጣት አመፅ አደንዲያደርጉ ቀስቅሰዋል በሚል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡rnrnመንግስት በሀገሪቱነ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና አክቲቪስቶች አመፁን በማባባስ ተግባር ለይ ተሰማርተዋል በማለት ወቀሳ አቅርቦባቸዋል፡፡rnrnየተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው  አባላት እና ደጋፊዎቻችን በምናንጋግዋ መንግስት  ሰዎች መዋከብ እና እንግልት እንዲሁም እስራ እየተፈፀመባቸው ነው በማለት መንግስትን ይከሳሉ፡፡rnrnበዚምባበቡየ የተፈጠረው የዋጋ ግሽበት የዜጎችን የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ አዳክሞታል ነው የተባለው፡፡

More in Africa