<strong>የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የኮንጎን የምርጫ ውጤት እየሞገተች ነው፡፡</strong>rnrnየኮንጎን የምርጫ ሂደት ከታዘቡት ተቋማት መካከል በሀገሪቱ ትልቅ ተሰሚነት ያላት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ናት፡፡rnrnይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያኗ የምርጫው ውጤት ሲገለፅ አሸናፊው እና እርሷ የታዘበቸው እውነታ እንዳልተገጣጠመላት በይፋ ተናግራለች፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የአፍሪካ ህብረት እና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ታዛቢዎችም የቤተ ክርስቲያኗን ሀሳብ ይጋራሉ፡፡rnrnነገር ግን የስልጣን ሽግግሩን ሰላማዊ ለማድረግ ህዝቡ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሆደ ሰፊ እንዲኑ ከመምክር የዘለለ መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል ነው የተባለው፡፡rnrnተቋማቱ ይህን ያደረጉት በሀገሪቱ ብጥብጥ እንዳይነሳ በመስጋት ሲሆን አንደንድ ዲፕሎማቶች ሌላኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ማርቲን ፋዩሉ በቀላሉ ማሸነፋቸውን ውስጥ ውስጡን እየተናገሩ ነው፡፡rnrnፋዩሉ በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ በምርጫ ኮሚሽኑ አሸናፊ ከተባሉት ፊሊክስ ሽሴኪዲ ጋር ተሻርከው ሀገሪቱን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ለመምራት የጎነጎት ሴራ ነው ብለዋል፡፡rnrnይህን ጥርጣሬ ያጎላው ደግሞ የምርጫው ውጤት በፊት ሁለቱ ወገኞች ስልጣን ለመጋራት በድብቅ ድርድር ያደርጉ ነበር የሚል ወሬ መሰማቱ ነው፡፡rnrnቤልጂየም እና ፈረንሳይም የምርጫ ውጤቱ እንዳስነገጣቸው እና ማብራሪያ የመጠየቅ ሀሳብ እንዳላቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው አማካይነት ተናግረዋል፡፡






