የኤርትራ የባህል እና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አዲስ አበባ ገባrnrnከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አንደሚጠቁመው ከ60 በላይ አባላት ያሉትና ታዋቂው አርቲስት በረኸት መንግስተአብን ጨምሮ የተለያዩ አከላትን ያካተተ የኤርትራ የባህልና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።rnrnቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርስ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተወከሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።rnrnየባህል ቡድኑ በቆይታው በኢትየጵያ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር የተለያዩ የባህል ዝግጅቶችን በማቅረብ የሁለቱን አገሮች የህብ ለህዝብ ትስስር የማጠናከር ስራ ይሰራል ሲል የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ገልፃል።rnrn






