የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኩባ ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር አንቶኒ ጋር ተወያዩ::rnrnአቶ ገዱ እና ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።rnrnበኢትዮጵያና በኩባ መካከል ያለውን ዘመናት ያሰቆጠረ ግንኙነት አጠናክረው ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩም መሪዎቹ ተናግረዋልrnrnበሁለቱ አገሮች መካከል በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በዲፕሎማሲ ዘርፍ ለዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በተሻለ ለማስቀጠል ይሰራልም ብለዋል አቶ ገዱ ። በተጨማሪም ሁለቱ አገሮች በቀጣይ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያላቸውን ትብብር የበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ም ተናግረዋል።rnrnየኩባው ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር አንቶኒዮ በበኩላቸው ሁለቱ አገሮች በሁለትዮሽና በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላቸው ትብብር ውጤታማ ነው ብለዋል። በቀጣይም ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትስስር አጠናክራ እንደምትቀጥልም ገልጸዋል፡፡rnrn
← NewsPolitics
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኩባ ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር አንቶኒ ጋር ተወያዩ::
Arts TV · ሜይ 30 2019





