Arts TVArts TV
← NewsPolitics

የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የድንበር ያለበትን ሁኔታ የሚገመግመዉ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡

Arts TV · ሜይ 17 2019

የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የድንበር ያለበትን ሁኔታ የሚገመግመዉ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የድንበር ያለበትን ሁኔታ የሚገመግመዉ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡rnrnየኢትዮ-ኬንያ የጋራ የድንበር ኮሚሽን ስብሳባ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች የችካል አጠባበቅ እና ግምገማ የሚያካሄዱበትን ቀነ-ገደብ ለማስቀመጥ ተስማምተዋል።rnrnከግንቦት 5 እስከ 9 ቀን በሞምባሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 32ኛው የኮሚሽኑ ጉባኤ በተጨማሪም ለስራው የሚያገለግል በጀትን የማሰናዳት ጉዳዮች ላይ ውይይት በማካሄድ በጀት አጽድቀዋል።rnrnበኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በስብሰባው ዝግጅት ላይ በመገኘት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፥ በወቅቱም በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል ያለው ግኑኝነት ታሪካዊ መሰረት ያለው እና ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።rnrnበተጨማሪም ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለረዥም ጊዜና ሳይቆራረጥ የመጣ መልካም የሁለትዮሽ ወዳጅነት እንዳላቸው በመግለፅ ይህ ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ወደ ላቀ የህዝብ-ለህዝብ ግንኙነት መሸጋገር እንዳለበት ገልጸዋል።rnrnሁለቱም ወገኖች ስምምነቶቹን ለመተግበር የሚያስችል ቃለ-ጉባኤ በልዑካን ቡድን መሪዎቻቸው አማካኝነት ተፈራርመዋል።rnየዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃላአቀባይ ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር እ.ኤ.አ 1950 እስከ 1955 መካለሉ የሚታወስ ነው።

More in Politics