የሳምንቱ መርሀግብር ጨዋታዎች ዛሬ ቀን 9፡00 ሰዓት ደደቢት እና ባህር ዳር ከነማ ትግራይ ላይ በዝግ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡rnrnበነገው ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ፤ ወላይታ ድቻ ወደ ትግራይ አቅንቶ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 9፡00 ላይ ይጎበኛል፡፡rnrnበአዲስ አበባ ስታዲየም 10፡00 ላይ ደግሞ መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ፡፡ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ስቱዋርት ሃልን ካሰናበተ በኋላ በምክትሉ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመራ የመጀመሪያ ግጥሚያውን ይጎበኛል፡፡rnrnዕሁድ ደግሞ አራት ግጥሚያዎች በክልል ስታዲየሞች በተመሳሳይ 9፡00 ላይ ሲከናወኑ፤ በ48 ነጥቦች የሊጉ አናት ላይ የተቀመጠው መቐለ 70 እንደርታ በትግራይ ስታዲየም ሀዋሳ ከተማን ያስተናግዳል፡፡ rnrnመቐለን በሁለት ነጥብ አንሶ የሚከተለው የጎንደሩ ፋሲል ከነማ ደግሞ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ይጫወታል፡፡ rnrnአዳማ ከተማ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ አምርቶ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ይፋለማል፡፡ rnrnወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ደቡብ ፖሊስ እና ስሑል ሽረ ሀዋሳ ላይ ይጫወታሉ፡፡ rnrnየሳምንቱ መርሀግብር የመዝጊያ ግጥሚያ በኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም 10፡00 ላይ ይከናወናል፡፡
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና በቀጣዮቹ ቀናት ይደረጋሉ፡፡
Arts TV · ሜይ 17 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019