Arts TVArts TV
← NewsSport

በኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡

Arts TV · ጁላይ 2 2019

በኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
የ2019 የኮፓ አሜሪካ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ዙር ላይ የደረሰ ሲሆን ዛሬ ከዕኩለ ሌሊት በኋላ በእኛ ሰዓት አቆጣጠር 9፡30 ሲል በሁለቱ ታላቅ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት አርጀንቲና እና ብራዚል መካከል ይከናወናል፡፡rnrnrnrnጨዋታው ቤሎ ሆሪዞንቴ በሚገነው በእስታዲዮ ሚኔሮ ሲደረግ ደስ ሚል የውድድር ጊዜ እያሳለፈች የምትገኘው አርጀንቲና በብራዚል ድል ልትደረግ እንደምትችል እየተዘገበ ይገኛል፡፡rnrnበኮፓ አሜሪካ 2019 ሩብ ፍፃሜ፤ የውድድሩ አስተናጋጅ ብራዚል በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ፓራጓይን 4 ለ 3 ፤ እንዲሁም አርጀንቲና ቬንዙዌላን 2 ለ 0 ድል በማድረግ ግማሽ ፍፃሜውን ተዋህደዋል፡፡rnrnየአልባሴልስቲዎቹ አምበል ሊዮኔል ሜሲ በውድደሩ በፍፁም ቅጣት ምት አንድ ጎል ብቻ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን የሚጠበቅበትን ያህል የጨዋታ እንቅስቃሴ እያደረገ እንዳለ ከብራዚሉ ጨዋታ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡rnrnየብራዚሉ ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫም፤ ሜሲ አሁንም የዓለም ምርጡ ተጫዋች በመሆኑ እና በየትኛው ጊዜ ምን እንደሚያደርግ ስለማይታወቅ በጥንቃቄ እንከታተለዋለን ሲል ተደምጧል፡፡  rnrnሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በኮፓ አሜሪካ ውድድር ከ2007 የፍፃሜ ጨዋታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን ያኔ ሴልካኦ 3 ለ 0 ድል ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡rnrnበኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ታሪክ ከባለፉት 45 ውድድሮች አስራ አራቱን በማንሳት ዩሯጓይን የምትከተለው አርጀንቲና ባለፉት አምስት የፍፃሜ ውድድሮች ውስጥ በአራቱ ላይ ተፋላሚ ብትሆንም በአንዱም ግን በለስ አልቀናትም፤ rnrnበአጠቃላይ በ14 ፍፃሜ ላይ በተቀናቃኞቿ ዋንጫውን ስትነጠቅ፤ ከ1993 በኋላ ደግሞ ይሄንን ድል ማጣጣም ተስኗታል፡፡ rnrnከ2007 በኋላ ዋንጫውን የማንሳት ዕድል ያልገጠማት ብራዚል በበኳሏ እራሷ በደገሰችው መሰናዶ የበይ ተመልካች ለላለመሆን ከፍፃሜ በፊት በሚደረገው የሱፐር ክላሲኮ የፍፃሜ ጨዋታ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት እያለመች በደጋፊዎቿ ፊት ትፋለማለች፡፡ rnrnምናልባትም ከሀገራቸው ጋር ይሄ የመጨረሻ ውድድራቸው ሊሆን ይችላል የሚባሉት ሊዮኔል ሜሲ እና ኩን አጉዌሮ በሌሊቱ ፍልሚያ የሞት ሽረት ትግል ሊያደርጉ እንደሚችሉ እየተነገረላቸው ይገኛል፡፡rnrnሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ ቺሊ እና ፔሩ በፖርቶ አሌግሪ ዕረቡ ሌሊት ይገናኛሉ፡፡        

More in Sport