የውድድሩ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ መከናወን የጀመሩ ሲሆን ዛሬ ምሽት እና በቀጣዮቹ ቀናት ይደረጋሉ፡፡rnrn
rnrnየውድደሩ አዘጋጅ ብራዚል አሬና ዶ ግሬሚዮ ላይ ፓራጓይን በ45 ሺ ተመልካቾች ፊት በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት አሸንፋ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀሏን አረጋግጣለች፡፡rnrnበመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ግብ ማስቆጠር ባለመቻላቸው ወደ ግማሽ ፍፃሜው የሚያልፈውን ቡድን ለመለየት በተሰጠው ፍፁም ቅጣት ምት ብራዚል 4 ለ 3 አሸንፋለች፡፡ rnrnፋቢያን ባልቡኤና ከፓራጓይ በኩል በቀይ ካርድ ከሜዳ ቢሰናበትም፤ ሴልካኦ ከ30 ደቂቃ በላይ ለሚበልጥ ጊዜ የነበራቸውን የቁጥር ብልጫ መጠቀም አልቻሉም፡፡rnrnበመለያ ፍፁም ቅጣት ምቱ ወቅት ዊሊያን፣ ማርኪንሆስ፣ ፊሊፔ ኮቲንሆ እና ጋብሪል ጄሱስ ለብራዚል ቢያስቆጥሩም ሮቤርቶ ፊርሚኖ አምክኗል፡፡rnrnየኮፓ አሜሪካ ሩብ ፍፃሜ ሁለተኛ ጨዋታ ደግሞ ዛሬ ምሽት ሲቀጥል በምድብ B አራት ነጥቦችን በመያዝ ሁለተኛ ሆና ያጠናቀቀችው አርጀንቲና ሪዮ ዴ ጄኔሮ በሚገኘው እስታዲዮ ዶ ማራካኛ በምድብ A አምስት ነጥብ በመሰብሰብ ብራዚልን ተከትላ ካጠናቀቀችው ቬንዙዌላ ጋር ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች፡፡rnrnበአሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የምትሰለጥነው አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ ፊት አውራሪነት እየተመራች ደካማ የውድድር ጊዜ እያሳለፈች ቢሆንም አሁንም ለሻምፒዮንነት ከሚጠበቁ ቡድኖች አንዷ ናት፡፡ rnrnበምሽቱ ጨዋታም ቬንዙዌላ ለአልባሴልስቲዎቹ ፈታኝ ልትሆን እንደምትችል ይጠበቃል፡፡rnrnየአርጀንቲና እና ቬንዙዌላ አሸናፊ በግማሽ ፍፃሜው ከብራዚል ይገናኛል፡፡rnrnሌሊት 8፡00 ሰዓት ላይ ደግሞ በምድብ B ላይ ሶስቱንም የጨዋታ መርኃግብር በድል የተወጣችው ኮሎምቢያ በአሬና ኮሪንታያንስ ከቺሊ ጋር ትጫወታለች፡፡ rnrnቺሊ ከምድብ C ሁለት ጨዋታዎችን በመርታት ስድስት ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ ሆና አጠናቅቃለች፤ ከካርሎስ ኪሮዧ ኮሎምቢያ ጋርም ብርቱ ትንቅንቅ ይኖራቸዋል ተብሎ እየተነገረ ይገኛል፡፡