Arts TVArts TV
← NewsAfrica

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኒው ዮርክ ታይምስን ዘገባ አጣጥሎታል፡፡

Arts TV · ማርች 22 2019

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኒው ዮርክ ታይምስን ዘገባ አጣጥሎታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኒው ዮርክ ታይምስን ዘገባ መሰረተ ቢስ ሲል አጣጥሎታል፡፡rnrnኒው ዮርክ ታይምስ አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪ ተገቢውን የምስለ በረራ ስልጠና አልወሰደም የሚል አንድምታ ያለው ዘገባ አሰራጭቷል፡፡rnrnአየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ በተለይ የአደጋው መንስኤ ገና እየተጣራ ባለበት ወቅት ይህን መሰል ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ማራጨት ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ማሳሳት ነው ብሏል፡፡rnrnፓይለቶቻችን አዳዲስ አውሮፕላኖች ባስመጣን ቁጥር ማብረር ከመጀመራቸው አስቀድሞ አስፈላጊውን ስልጠና ከአምራች ኩባንያው በሚሰጠው ማሳሰቢያ እና ኤፍ ኤኤ ባፀደቀው መሰረት ስልጠናዎችን ወስደዋል ብሏል ተቋሙ፡፡rnrnኒው ዮርክ ታይምስ ለአየር መንገዱ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን አናገርኩ ብሎ ያሰራጨው ዘገባ የተዛባ መሆኑንም አስታውቋል፡፡rnrnበአሁኑ ጊዜ የኢትየጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ህጉ በሚያዘው መሰረት የመረጃ ትንተናውን ውጤት በትግእስት እየተጠባበቀ መሆኑን ተናግሯል፡፡rnrnበተለይ በኢንዶኔዥያ አደጋ ከደረሰ በኋላ የአሜሪካው ኤፍ ኤኤ ያወጣውን መመሪያ ሁሉም አብራሪዎች እንዲያውቁት አስፈላጊው ገለፃ ከመደረጉም ባሻገር የመመሪያው ሙሉ ይዘት በስልጠና ማንዋል ተካቷልም ብሏል አየር መንገዱ፡፡rnrnከዚህ በኋላም ቢሆን ሁሉም የመገናኛ ብዙሀን የምርመራ ውጤቱ ተጠናቅቆ ለህዝብ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ከመሰል አሳሳች ዘገባዎች መቆጠብ እንዳለባቸው ጥሪውን አቅርቧል፡፡

More in Africa