Arts TVArts TV
← NewsAfrica

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና የፈረንሳዩ ብሄራዊ የስፔስ ጥናት ማዕከል በጋራ ሊሰሩ ነው

Arts TV · ማርች 14 2019

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና የፈረንሳዩ ብሄራዊ የስፔስ ጥናት ማዕከል በጋራ ሊሰሩ ነው

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና የፈረንሳዩ ብሄራዊ የስፔስ ጥናት ማአከል በህዋ ሳይንስ ዘርፍ በጋራ ሊሰሩ ነው፡፡rnrnተቋማቱ በጋራ ለመስራ የሚስችላቸውን ስምምነት ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡rnስምምነቱ ከሳተላይት የሚገኙ የአየር ንብረት መረጃዎችንና መተግሪያዎችን በመጠቀም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅኖዎችን በዘላቂነት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ክትትል ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡rnየህዋ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እርሻን፤ የደን ሽፋን፤ ውሃ የሚገኝባቸውን አካባቢ መለየትና መከታተል የሚያስችሉ ተግባራትን መከወን የሚያስችል እና ሌሎች ተግባራትንም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡rnrnየሰው ሃይል አቅም ግንባታና ልውውጥ፤ የህዋ ሳይንስን ለሰላማዊ ግልጋሎት መጠቀም የሚያስችል የትብብር ዘርፍ እንዲኖር ማዕቀፍ መፍጠር፤ የትብብር መስኮች ወደ ትግበራ የሚገቡበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸትም የስምምነቱ አካል  ናቸው ተበሏል ፡፡rnrnስምምነቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር  ዶክተር ሰለሞን በላይ እና የፈረንሳዩ ብሄራዊ የስፔስ ጥናት ማአከል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጄን-የቭስ ሊ ጋል  ፈርመውታል፡፡rnrnበሂልተን ሆቴል የተካሄደው የስምምነት ፊርማ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርጉት የትብብር ስምምነት አካል መሆኑ ተነግሯልrnዘገበው የኢኖቪሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡

More in Africa