የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቋልrnrnስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በድርጅታዊ እና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዩች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔዎችን አሳልፏል ቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል ተብሏል፡፡rnrnየሃገሪቱ ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይት በኢኮኖሚው ዘርፍ ማሻሻይዎች ላይ የቀረቡ ሰኖዶችን ገምግሟል ነው የተባለው፡፡rnrnበሃገሪቱ ባለፉት 12 ወራት የተደረጉ የኢኮኖሚ በተለይም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ የተወያየው ኮሚቴው ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት መቀዛቀስዝ ስለመከሰቱ ገልጿል፡፡rnrnየውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የውጭ እና የውስጥ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባት፣ የስራ ዕድል አለመፈጠር፣ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፉ ላይ የታዩ ክፍተቶች ለኢኮኖሚው መቀዛቀዝ እንደ ምክንያት ተነስቷል ሲል የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት በገፁ አስፍሯል፡፡rnrnበመሆኑም የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ ያላቸውን ሚና በመወሰን ቀጣይ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ የሚያደርጉ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል ተብሏል፡፡rnrn rnrn rnrn





