የአፍሪካ ህብረት ሱዳንን ለጊዜው ከአባልነት እንቅስቃሴዋ አገደ፡፡rnrnህብረቱ በአስቸኳይ ስብሰባው በሱዳን የተጀመረው ድርድር በሰላም እስኪጠናቀቅ ሱዳን በአባልነቷ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርግ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው፡፡rnrnገልፍ ኒውስ እንደዘገበው በሱዳን በሲቪሎች የሚመራ መንግስት ካልተመሰረተ ከህብረቱ አባልነቷ ታግዳ ትቆያለች፡፡rnrnየአፍሪካ ህብረት የፀጥታው ምክር ቤት በሱዳን በሲቪል የሚመራ መንግስት እንዲቋቋም በወታደራዊ ምክር ቤቱ እና በተቃዋሚዎች መካከል የተጀመረው ውይይት በፍጥነት እንዲጀመር አሳስቧል፡፡rnrnበመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ለሳምንታት ተቃውሟቸውን እያሰሙ የከረሙ ሰዎችን ለመበተን በተደረገ ሙከራ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ





