የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡrnrnየሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ሙሀመድ "ፋርማጆ" ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።rnrnቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።rnrnበአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደክተር ወርቅነህ ገበየሁን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።rnrnከዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት እንደገለጸዉ ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽና በክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ።rnrnጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአፍሪካ ቀንድ ክልላዊ ሰላም ለማስፈንና የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር የጀመሩት ዲፕለማሲያዊ እንቅሰቃሴ አካል በሆነው በዚህ ጉብኝት በክልሉና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።rnrnፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ መሐመድ በኢትየጵያ በአንድ ቀን በሚኖራቸው ቆይታ ባላፉት ቀናት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኬንያ ፕሬዝዳንት ኡህሩ ኬንያታ፣ ከኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንዲሁም ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ጋር ካደረጓቸው የሁለትዮሽና የሶስትዮሽ ውይይቶች የቀጠለ በቁልፍ ቀጣናዊና የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።rnrn rnrn rnrn






