የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ዜግነት በቃኝ አሉ ፡፡rnrnፕሬዝዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ አሜሪካ የሰጠቻቸውን ዜግነት በፈቃዳቸው መሰረዛቸውን ቢናገሩም ለምን እዚህ ውሳኔ ላይ እንደደረሱ ግን ይፋ አላደረጉም፡፡rnrnፋርማጆ ጉዳዩን ከጠበቆቻቸው ጋር በመሆን መጨረሳቸውን ከፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት የወጣ መረጃ ያሳያል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የሶማሊያ ህገ መንግስት ጥምር ዜግነት የሚፈቅድ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ግን ሁለቱንም ዜግነት ይዘው መቀጠል አልፈለጉም፡፡rnrnረዘም ላለ ጊዜ ኑሯቸውን በአሜሪካ ካደረጉ በኋላ ተመልሰው ሀገራቸውን እያገለገሉ ያሉት ፕሬዝዳንቱ በቀጣዩ ምርጫም ዳግም መፎካከር እንደሚፈልጉ ተነግሯል፡፡rnrnፋርማጆ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የሀገሬን ህዝብ በማገልገሌ ታላቅ ኩራት ይሰማኛል፤ሶማሊያዊያን ሀገራችንን ተባብረው ዳግም ታላቅ እንደሚያደርጓት አልጠራጠርም ብለዋል፡፡rnrnፋርማጆ ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት ማገልገል ከጀመሩ ወዲህ ከአልሸባብ ጋር በሚያደርጉት ውጊያ አሜሪካ ከጎናቸው አልተለየችም፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙrnrn





