የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በተማሪዎች ሞት አዝኛለሁ አለ፡፡rnrnየሽግግር ምክር ቤቱ መሪ ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሀን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሰሜናዊ ኮርዶፋን አል ኦቤይድ ከተማ የተፈፀመው የአምስት ተማሪዎች ግድያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው ተማሪዎቹ የነዳጅ እና የዳቦ ዋጋ አሻቀበ በሚል ምክንያት ለተቃውሞ አደባባይ በመውጣታቸው ነው በፀጥታ ሀይሎች የተገደሉት፡፡rnrnአልቡርሀን ድርጊቱ ወንጀል መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩ በአስቸካይ ተጣርቶ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡rnrnተቃዋሚዎቹ በወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ምክትል ሀላፊ ጄኔራል ሞሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ እዝ ስር የሚንቀሳቀሰው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ነው ይህን ግድያ የፈፀመው ሲሉ ይከሳሉ፡፡rnrnዳጋሎ ግን ይህ በሚሆንበት ጊዜ ለስራ ጉብኝት ወደ ካይሮ አቅንተው ከፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ጋር እየተወያዩ ነበር ተብሏል፡፡rnrnምክር ቤቱ ይህን መግለጫ የሰጠው ተቃዋሚዎቹ በቅርቡ በሲቪል መንግስት ምስረታ ዙሪያ ከጄኔራሎቹ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ውይይት መሰረዛቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው የሚል ዘገባ በሰፊው እየተሰራጨ ነው፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙrnrn





