የሱዳን አመፅ ከአረብ አብዮት የተቀዳ ስለመሆኑ አልበሽር ፍንጭ ሰጡ፡፡rnrnአልበሽር ይህን ያሉት በሀገራቸው አመፁ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ሁለተኛ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በጎረቤት ግብፅ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡rnrnፕሬዝዳንቱ ነገሩን ከረአብ አብዮት ጋር ያገናኙት የዳቦ ዋጋ ጨመረብን ብለው ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች አጀንዳቸውን ቀይረው አልበሽር ከሰልጣን ይውረዱ ይህ ካልሆነ ግን ወደ ቤት በማለታቸው ነው፡፡rnrnየሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር 30 ዓመት በሚጠጋው የአስተዳደር ዘመናቸው እንዲህ ዓይነት ጠንካራ ተቃውሞ ደርሶባቸው አያውቅም ተብሏል፡፡rnrnአልበሽር ተቃውሞው በተበባሰበት ሰሞን የኢኮኖሚ መሻሻያዎችን ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር፡፡ ግን ደግመሞ በሀገሪቱ የተከሰተው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አላለውስ ቢላቸው ወደ ኳታር ተጉዘው የኳታሩን አሚር እርዳታ ጠይቀዋል፡፡rnrnይሁን እንጂ አሁን በሱዳን እየተነሳ ያለው ጥያቄ የዳቦ ዋጋ ይቀንስ ሳይሆን አልበሽር ይውዱ የሚል ስለሆነ ኳታር እጇን ብትዘረጋ እና የተባለው ማሻሻያ ተግባራዊ ቢሆ እንኳ እርምጃውን የዘገየ ነዉ ይላሉ ይላሉ የፖለቲካ አዋቂዎች፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልታህ አልሲሲ ሱዳን ወደተረጋጋ ህይዎት እንድትመለስ አልበሽርን ለማገዝ ዝግጁነታቸውን ነግረዋቸዋል፡፡






