የመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በሀገር ሽማግሌዎች መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ አስታወቀ፡፡rnrnየመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በተፅእኖ ፈጣሪ የሀገር ሽማግሌዎች መፍትሄ ሰጪነት መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ ገልጿል፡፡rnrnበመተከል ዞን ሰሞኑን የተከሰተው የሰብአዊ ቀውስና የፀጥታ ችግር የሚፈታው ከነዋሪዎች በሚመነጭ የሰላም ፍላጎት እና በተፅእኖ ፈጣሪ የሀገር ሽማግሌዎች መሆኑም ተነግሯል፡፡rnrnየአገው ብሔራዊ ሸንጎ ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ እንደገለፀው የጉምዝ ፤ የሽናሻ ፤ የኦሮሞ እና የአማራ ህዝቦች የአንድነትን እና አብሮ የመኖር ባህልን የተላበሰ ማህበረሰብ ነው ያለ ሲሆን ፤ ሰሞኑን በተከሰተው ሰብአዊ ቀውስና የሰው ህይወት ህልፈት ሸንጎው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፃôል፡፡rnrnበመተከል ዞን ግጭት እንዲፈጠር ያደረጉ ሃይሎች ድብቅ አለማቸውን በህዝብ ደም ለማሳካት የሚሞክሩ ፅንፈኛ ሃይሎች የፈጠሩት እንደሆነ በመግለፅ፤ ሸንጎው እነዚህ ሀይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡rnrnየመከላከያ ወደ አካባቢው መግባትን የገለፀው ብሔራዊ ሸንጎው ፤ የመከላከያ ወደ አካባቢው መግባት ችግሩን ለመፍታት መልካም ቢሆንም ለችግሩ ፀጥታ መረጋገጥና ዋንኛ መፍተሄ ለማምጣት ከመተከል ህዝብ የሚቀድም የለም ብሏል ፡፡rnrnበመሆኑም ከሁለቱም ክልሎች እና ከተሞች የሀገር ሽማግሌዎችን በመላክ ችግሩ ወደ ተከሰተባቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች በመላክ ከፀጥታ አካለት ጋር በመተባበር ባህላዊ የእርቅ አና የግጭት አፈታት ስርዓትን በመከተል ችግሮችን የመፍታት ስራ እንዲሰሩ ሸንጎው ጥሪ አቅርቧል፡፡rnrnይህ በእንዲህ እንዳለ የቢንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዜጎቹን ሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለማሰጠበቅ የተማôላ ህገ መንግስታዊ ስልጣን ያለው በመሆኑ ትንኮሳን አደብ ሊያስገዛ እንደሚገባ ሸንጎው አሳስቧል፡፡rnrnበመጨረሻም በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ምክንያት ከቤት ንበረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎቸን ወደነበሩበት ለመመለስ ከሚመከለከታቸው አካለት ጋር በጋራ እየሰራ እንሚገኝም ነው ሸንጎው በመግለጫው የጠቆመዉ፡፡rnrn
← NewsPolitics
የመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በሀገር ሽማግሌዎች መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ አስታወቀ፡፡
Arts TV · ሜይ 7 2019





