Arts TVArts TV
← NewsAfrica

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀች

Arts TV · ጃን 15 2019

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀች

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀችrnrnኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ያካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ፉክክር የድምፅ ቆጠራ ውጤት ይፋ ቢደረግም፤ በተፎካካሪዎች ዘንድ የተሳሳተ ነው መባሉን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ)  የድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታከናውን ጥሪ አቅርቦላታል፡፡rnrnኮንጎ ነፃነቷን ከተቀዳጀች ከ59 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ማብሰሪያ  ይሆናል ብሎ ተስፋ የተጣበት ምርጫ ከሁለት ሳምንት በፊት ተካሂዶ ነበር፡፡rnrnየተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ፊሊክስ ሸሲኪዲ እና ካቢላ ጥምረት ፈጥረው አሸናፊነታቸውን ሊያውጁ ነው ቢባልም የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን  ሽስኬዲ በጠባብ የድምፅ ብልጫ ማርቲን ፋዩሉን አስከትለው አሸንፈዋል ሲል ይፋ አድርጓል፡፡rnrnበምርጫው ተፎካካሪ የነበሩት እና በተሰጠው ድምፅ ሁለተኛ የወጡት ፋዩሉ ግን አሸናፊነት ይገባኛል እያሉ ነው፡፡rnrnሽስኬዲ እና ካቢላም ስለ ተባለው ጥምረት አስቀድመው አሉባልታ ነው ብለዋል፡፡rnrnየኮንጎ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደግሞ በምርጫው ያሰማራኋቸው 40 ሺ ጠንካራ ታዛቢዎቼ ያደረሱኝ የድምፅ ውጤት አሸናፊ ኮሚሽኑ ይፋ ካደረገው የተለየ ነው ብላለች፡፡rnrnሳድክ ባወጣው መግለጫም በአሸናፊዎቹም ሆነ ተሸናፊዎች ወገን መተማመን ለመፍጠር ሲባል የድምፅ ቆጠራው በድጋሜ ቢደረግ የሚል ነው፡፡rnrnሳድክ የካቢላ አጋር አንጎላን እና ደቡብ አፍሪካን የመሳሰሉ ሀገራትን ያቀፈ ሲሆን የካቢላ፣ ፋዩሉ እና ሽሲኬዲ የሚወክሏቸው ፓርቲዎች ለሀገሪቱ ብሔራዊ ህብረት ሲባል ሰላምን እንዲዘምሩ አሳስቧል፡፡rnrnይሁን እንጂ ይህ አይነቱ ህብረት በኮንጎ የሚታይ አይመስልም፡፡ ምክንያቱም የካቢላ ቀንደኛ ተቀናቃኝ ፋዩሉ ይፋዊ ቅሬታቸውን በሳምንቱ መጨረሻ  ለሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት አስገብተዋል ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

More in Africa