ናይጄርያ ዜጎቿን እናንተ ድምፅ ስጡ አንጂ መጓጓዣውን ለኔ ተውት ብላለች፡፡rnrnየናይጄሪያ ነዳጅ አቅራቢዎች የታክሲና አውቶቡስ ሹፌሮች፣ እንዲሁም የአየር መንገዶች በመጪው ቅዳሜ በሜካሄደው ምርጫ ድምፅ ለመስጠት ከተለያዩ ቦታዎች ለሚመጡ መራጮች የታሪፍ ቅናሽ ሊያደርጉ ነው፡፡rnrnየድምፅ ሰጪዎች ቁጥር አነስተኛ እንዳይሆን ያሳሰባቸው የሁለቱም ተፎካካሪ ወገኖች በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ እና ለመምረጥ የተመዘገቡት ነዋሪዎች እንዳይቸገሩ በማሰብ ነዉ ይህን ያደረጉት፡፡rnrnፓርቲዎቹ ከምርጫ ጣቢያዎች እስከ መኖሪያቸው ድረስ ለመጓዝ አቅሙ ለማይፈቅድላቸው ነዋሪዎች የትራንስፖርት ወጪያቸው ላይ ቅናሽ ለማድረግ ስምምነት አድርገዋል፡፡rnrnበመጪው ቅዳሜ የሚደረገው የናይጄርያ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ 84 ሚሊዮን ሰው ድምፅ ለመስጠት መመዝገቡን የናይጄርያ የምርጫ ኮሚሽን ገልጿል፡፡rnrnየኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ሊይ መሀመድ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት 2 ሚሊዮን አባለት ያሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰራው የትራንስፖርት ባለስለጣን መራጮችን ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ቀና ትብብር አሳይቷል፡፡rnrnነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶችም የነዳጅ ዋጋን ከ 145 ወደ 140 ናኤራ በሊትር ዝቅ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ በዘገባው ሁለት አየር መንገዶችም ከተለያዩ ሀገራት ድምፅ ለመስጠት ለሚንቀሳቀሱ ዜጎች ድምፅ መስጫ ካርዶቻቸውን ብቻ በማየት ቅናሽ ማድረጉን አስነብቧል፡፡rnrnየናይጄርያው ፕሪዝዳንት ሙሀማዱ ቡሃሪ የሀገሪቱን የነዳጅ ሃብት ከሙሰኞች እጅ ለማውጣት እና በሀብታም እና ደሀ መሀከል ያለውን ልዩነትት ለማጥፋት የሚለውን አቋማቸውን አሁንም ለቅስቀሳ ተጠቅመውበታል፡፡rnrnተፎካካሪያቸው አቲኩ አቡበከር ደግሞ በናይጄርያ ያለውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ተናገረዋል፡፡rnrn rnrn






