Arts TVArts TV
← NewsPolitics

ትራምፕ ስደተኞችን ችሎታ እና እድሜ ላይ ባተኮሩ መስፈርቶች እንቀበላን አሉ፡፡

Arts TV · ሜይ 17 2019

ትራምፕ ስደተኞችን ችሎታ እና እድሜ ላይ ባተኮሩ መስፈርቶች እንቀበላን አሉ፡፡

ትራምፕ ስደተኞችን ችሎታ እና እድሜ ላይ ባተኮሩ መስፈርቶች እንቀበላን አሉ፡፡rnrnበስደተኞች ጉዳይ በብጥቅየሚተቹት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ  ሀገራቸው ስደተኞችን  የምትቀበልበት አዲስ ፖሊሲ ለማውጣት አቅደዋል፡፡rnrnበዚህም መሰረት ወደ አሜሪካ ለመግባት አንዱ መለኪያ ወጣትነት  እንደሆነ ከዋይት ሀውስ የወጣው መረጃ ያሳያል፡፡rnrnቢቢሲ እንደዘገበው ወጣት መሆን በራሱ ግን ብቸኛ መስፈርት አይደለም፡፡ በተጨማሪም በትምህርታቸው የገፉ እና እንግሊዘኛን አቀላጥፈው የሚናገሩ ሰራተኞች አሜሪካ ገብተው እንዲሰሩ ይበረታታሉ በአዲሱ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ፡፡rnrnትራምፕ ይህን ትልቅ ለውጥ የምናደርገው ወደ ሀገራችን ገብተው በእውቀት እና  በክሎታቸው ውጤታማ ስራ የሚሰሩ ሰዎችን ቁጥር ለማብዛት  ነው ብለዋል፡፡rnrnበፕሬዝዳንቱ የቀረበው አዲሱ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ተግባራዊ ከሆነ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞች ከትምህርት እና ከእንግለዝኛ ችሎታ በተጨማሪ የሲቪክስ ፈተና ወስደው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡rnrnአዲሱ የትራምፕ እቅድ የሪፓብሊካን ፓርቲ ተወካይ ከሆኑት የምክር ቤት አባላት  ተቃውሞ ቀርቦበታል፡፡rnrnለተቃውሟቸው አንዱ ምክንያት አዲሱ የፖሊሲ እቅድ አሜሪካ የሚገኙ 11 ሚሊዮን ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን አያካትትም የሚል ነው፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Politics