የአውሮፓ ቻምዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ሌላ ጨዋታ ስፔን ላይ ሲካሄድ ባርሴሎና በኑ ካምፕ የእንግሊዙን ሊቨርፑል ያስተናዳል፡፡rnrnበሩብ ፍፃሜው ባርሳ ሌላኛውን የእንግሊዝ ቡድን ጥሎ፤ ሊቨርፑል ደግሞ የፖርቱጋሉን ፖርቶ አሰናብቶ ነበር ወደ ግማሽ ፍፃሜው ዙር የተቀላቀሉት፡፡ rnrnሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም ተገናኝተው ሊቨርፑል በባለፉት አራት ከሜዳው ውጭ ጨዋታዎች ሽንፈት አያውቅም፡፡ ከእንግሊዝ ክለቦች በተሻለም ቀያዮቹ በካታላኑ ቡድን ላይ ከሜዳ ውጭ ጨዋታ ላይ ድል በማመዝገብ ስም አላቸው፡፡ rnrnባርሴሎና ግን አሁንም ለፍፃሜው ይደርሳል ተብሎ ቀዳሚ ግምት የተሰጠው ቡድን ነው፡፡rnrnዛሬ ምሽት 4፡00 በሚጀምረው ጨዋታ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ጉዳት የነበራቸው ብራዚላውያኑ ሮቤርቶ ፊርሚኖ እና ፋቢንሆ ሊሰለፉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡rnrnየዘንድው የላሊጋ ውድድር ሊጠናቀቅ የሶስት ሳምንታት ጨዋታዎች ቢቀሩም ባርሴሎናዎች 26ኛ የላሊጋ ድላቸውን አስቀድመው ማሳካታቸውን ተከትሎ ከደስታ መልስ ሌላኛውን ታላቅ ክብር ለማከል እያለሙ የምሽቱን ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡rnrnየአርጀንቲናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ እና ሆላዳዊው ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ ትንቅንቅ በምሽቱ ይጠበቃል፡፡rnrnብራዚላዊው ፊሊፕ ኮቲንሆ እና ሊዊስ ሱዋሬዝ የቀድሞ ክለባቸውን በተቃራኒ ማሊያ ይገጥማሉ፡፡
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
ተጠባቂው የባርሴሎና ሊቨርፑል የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ ዛሬ ምሽት ይከወናል
Arts TV · ሜይ 1 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019