ቡሃሪ ለሁለተኛ ዙር የምርጫ ቅስቀሳቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡rnrnየናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ሙሀማዱ ቡሀሪ በሰሜናዊ ናይጀሪያ በምትገኘው ትልቋ የኢኮኖሚ ከተማ ካኖ በአስር ሺህዎች በሚቆጠሩት ደጋፊዎቻቸው ፊት ቀርበው ነው ለዳግም ምርጫ መጥቻለሁ ተዘጋጁ ያሉት፡፡rnrnቡሀሪ በተደጋጋሚ በህመም ምክንያት ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር መመላለስ ማብዛታቸው እና ከስራ የሚርቁበት ጊዜ በመብዛቱ ተፎካካሪዎቻቸው ለስራው ብቁ አይደሉም በማለት ይከራከራሉ፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከኒጀር የመጡ የአውራጃ አስተዳዳሪዎች በስነ ስርዓቱ ላይ መገኘታቸውን ተቃውሟ፡፡rnrnምክንያቱ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ከአሁኑ የምርጫውን ውጤት በጎረቤት ወዳጆቻቸው ድጋፍ ለማስቀየር እየተዘጋጁ ነው የሚል ነው፡፡rnrnቡሀሪ ለሁለተኛ ጊዜ ከመረጣችሁኝ በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ እንዲሁም ኢኮኖሚያችን እንዲያድግ ተግቼ እሰራለሁ ማለታቸውም ተሰምቷል፡፡rnrnፕሬዝዳንቱ በመጀመሪያው ዙር የስልጣን ቆይታቸው ሙስንን እና ቦኩ ሀራም የተባለውን ታጣቂ ቡድን ለማጥፋት የገቡትን ቃል አልፈፀሙም ተብለው ይወቀሳሉ፡፡rnrn rnrn rnrn rnrn





