Arts TVArts TV
← NewsAfrica

ሶማሊያ ውስጥ በቦንብ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 19 2019

ሶማሊያ ውስጥ በቦንብ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

ሶማሊያ ውስጥ በቦንብ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡rnrnየሀገሪቱ ፖሊስ በሰጠው ማረጋገጫ ሞቃዲሾ ውስጥ በተሸከርካሪ ላይ በተጠመደ ፈንጂ  አራት ሰዎች ህይዎታቸው ሲያልፍ አምስቱ ደግሞ ቆስለዋል፡፡rnrnሲ ጂ ቲ ኤን የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው መካ አል ሙከረማ በተባለው የከተማዋ ክፍል ከባድ  የፍንዳታ ድምፅ የሰሙ ነዋሪዎች በእጂጉ ተደናግጠው ነበር፡፡rnrnአንድ የግል የአምቡላንስ ድርጂት ዳይሬክተር የሆኑት ሞሀመድ አብዲከሪም ደግሞ አንድ አስከሬን እና 13 ቁስለኞችን ወደ ሆስፒታል ማጓጓዛቸውን ተናግረዋል፡፡rnrnባለፈው መጋቢት ወር ላይ ሞቃዲሾ ውስጥ በአንድ ምግብ ቤት እና መንግስት ባለ ስልጣናት መኖሪያ ህንፃ ላይ በደረሱ የቦንብ አደጋዎች 30 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Africa