Arts TVArts TV
← NewsPolitics

ሱዳን በ11 አባላት የሚመራውን አዲሱን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሰረተች፡፡

Arts TV · ኦገስ 21 2019

ሱዳን በ11 አባላት የሚመራውን አዲሱን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሰረተች፡፡

ሱዳን በ11 አባላት የሚመራውን አዲሱን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሰረተች፡፡rnrnየሱዳን ተቃዋሚዎች እና ጊዜያዊ ወታደራዊ ምክር ቤት ለወራት ከተደራደሩ በኋላ ለሶስት ዓመት ሀገሪቱን የሚመራውን ምክር ቤት በይፋ መስርተዋል፡፡rnrnምክር ቤቱን በበላይነት የሚመሩት አባላቱ አምስቱ ከጦር ሀይሉ አምስቱ ከተቃዋሚዎቹ የተውጣጡ ሲሆኑ አንደኛው ደግሞ ሁለቱ ተስማምተው በጋራ የመረጡት ነው ተብሏል፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው አዲሱ ምክር ቤት ለሶስት ዓመታት ሀገሪቱን ከመራ በኋላ ሀገራዊ ምርጫ ተካሂዶ የሲቪል መንግስት ይአንዲቋቋም ነው ሁለቱ ወገኖች የተስማሙት፡፡rnrnምክር ቤቱ ከተመሰረተ ማግስት ጀምሮ የሚቀጥሉትን 21 ወራት ከወታደራዊ ምክር ቤቱ የተወከሉት ሌተናል ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሀን የሚመሩት ሲሆን ቀሪዎቹን 18 ወራት ደግሞ ተቃዋሚዎቹ ይመራሉ፡፡rnrnወታደራዊ ምክር ቤቱ እና ተቃዋሚዎቹ ተስማምተው በጋራ ለሶስት ዓመት የሚያስተዳደርሩት የሽግግር ካውንስል 300 የሚሆኑ ህግ አውጭ አባላት እንደሚኖሩትም ታውቋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Politics