ሱዳናዊያን በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ውይይት መፍታት ይበጃቸዋል ሲሉ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡrnrnምክተል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየመከረ ባለው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ውይይት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።rnrnምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ንግግራቸው የሱዳን ፖለቲከኞችና ባለድርሻ አካላት በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ውይይት መፍታት እንደሚገባቸው ነው ምክራቸውን የለገሱት።rnrnምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በንግግራቸው ኢትዮጵያ በሱዳን አሁን የተከሰተውን አስቸጋሪ ሁኔታ በጥበብ በመፍታት የሱዳንን ሉኣላዊነት እና ነፃነት እንደሚያስጠብቁ በሱዳን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሙሉ እምነት አላት ነው ያሉት።rnrnበዚህም ኢትዮጵያ የሱዳንን ህዝብ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ገልጸው፣ በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ያለ መግባት መርህን ትከተላለችም ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።rnrnምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም በአፍሪካ ህብረት የተዘጋጀውን የውይይት መድረክ ኢትዮጵያ እንደምትደግፍ ገልጸው፣ ኢትዮጵያ እንደ ኢጋድ ሊቀመንበርነቷና እንደ አፍሪካ ህብረት አባልነቷ ለችግሩ አፍሪካዊ መፍትሄ ለመሻት በሙሉ አቅሟ እንደምትሰራም አስታውቀዋል።rnrnስብሰባው የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በሆኑት የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ አማካኝነት የተመራ ሲሆን፤ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማትን ጨምሮ የጅቡቲ፣የኬንያ፣የሶማሊያ፣የሩዋንዳ እና የደቡብ ሱዳን መሪዎች በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።rnrn rnrnበዚሁ ስብሰባ የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ ውሳኔ ተላልፏል።rnrnበተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ከዚህ በፊት ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ የቀረው የአንድ ሳምንት ጊዜ ብቻ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እንዲችል ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ውሳኔ ተላልፏል።rnrnከህብረቱ ስብሰባ አስቀድሞ በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ሊቀመንበር በሆነችው ኢትዮጵያ የተመራው የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ውይይት ተካሂዷል።
← NewsAfrica
ሱዳናዊያን በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ውይይት መፍታት ይበጃቸዋል ሲሉ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ
Arts TV · ኤፕሪ 24 2019