ሩዋንዳ እና ዩጋንዳ በመካከለላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ማርገብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡rnrnየዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና የሩዋንዳው አቻቸው ፖል ካጋሜ አንጎላ ውስጥ ተገናኝተው ነው ስምምነቱን የተፈራረሙት፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው ሁለቱ ተጎራባች ሀገራት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዷ ሌላዋን ሰለልሽኝ በማለት በተደጋጋሚ ሲካሰሱ ነበር፡፡rnrnበዚህም የተነሳ በጎረቤታሞቹ የድንበር አካባቢ የነበረው የንግድ እና የሰዎች ለሰዎች ግንኙነት እንቅስቃሴ እክል ገጥሞት ቆይቷል፡፡rnrnሩዋንዳ ጎረቤት ዩጋንዳን መሰረታቸውን ካምፓላ ያደረጉትን የሩዋንዳ ነፃነት እና ዲሞካራሲያዊ ሀይሎች የተባሉ ተቀናቃኞቸን በመደገፍ ተግባር ላይ ተሳትፋለች ብላ ከሳት ነበር፡፡rnrnከዩጋንዳ በኩልም በሩዋንዳ ላይ የተለያዩ ክሶች ሲሰነዘሩ የነበረ ሲሆን አሁን ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት ስምምነት አንዱ የሌላውን ጠላት ላለመደገፍ፣ እንዲሁም የድንበር አካባቢ እንቅስቃሴዎች ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሚለውን ያካትታል፡፡rnrnነፍጥ አንግበው የየሀገራቸውን መንግስታት በመውጋት ሰራዊታውን እየመሩ በሀይል ወደ ስልጣን የመጡት ካጋሜ እና ሙሴቬኒ ለዓመታት የልብ ወዳጆች የነበሩ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በመካከላቸው ነፋስ ገብቷል ነው የተባለው፡፡rnrnከፊርማው ስነስርዓት በኋላ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ንግግር የተፈረመውን ስምምነት ለማክበር እና ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ
← NewsPolitics
ሩዋንዳ እና ዩጋንዳ በመካከለላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ማርገብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
Arts TV · ኦገስ 22 2019





