በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል/ፊፋ ስር የሚተዳደረው እና ከዛሬ 28 ዓመት በፊት በ1991 ዓ/ም የተጀመረው የፊፋ ሴቶች የዓለም ዋንጫ ውድድር በየዓራት ዓመቱ እየተከናወነ ቆይቶ፤ ዛሬ 8ኛው ውድድር በፈረንሳይ አስተናጋጅነት ይጀመራል፡፡rnrn
rnrnበ24 ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ይሄ ውድድር ዛሬ ምሽት ሲጀመር በመክፈቻው ጨዋታ ምድብ አንድ ላይ የውድድሩ አዘጋጅ ፈረንሳይ እና ደቡብ ኮሪያ ይገናኛሉ፡፡ ጨዋታው ምሽት 4፡00 ላይ በፓርክ ደ ፕሪንስ ስታዲየም ይጀመራል፡፡rnrnበውድድሩ ከስድስት ኮንፌዴሬሽኖች የተወጣጡ 24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል ዘጠኝ ከተሞች ላይ በሚገኙ ዘጠኝ ስታዲየሞች ላይ የሚፎካከሩ ይሆናል፡፡rnrnአፍሪካ በሶስት ብሔራዊ ቡድኖች ስትካፈል ካሜሮን፣ ናይጀሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ይሄንን ዋንጫ ወደ አህጉሩ ለማምጣት ይተጋሉ፡፡rnrnበውድደሩ ከምድብ አንድ ፈረንሳይ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኖርዌይ እና ናይጀሪያ ይገኛሉ፤ ከምድብ ሁለት ጀርመን፣ ቻይና፣ ስፔን እና ደቡብ አፍሪካ ይፎካከራሉ፤ rnrnከምድብ ሶስት አውስትራሊያ፣ ጣሊያን፣ ብራዚል እና ጃማይካ አሉበት፡፡ rnrnከምድብ አራት እንግሊዝ፣ ስኮትላንድ፣ አርጀንቲና እና ጃፓን ይገኛሉ፡፡rnrnከምድብ አምስት ካናዳ፣ ካሜሮን፣ ኒው ዚላንድ እና ኔዘርላንድስ ተመድበዋል፡፡ rnrnከመጨሻው ምድብ ስድስት ደግሞ አሜሪካ፣ ታይላንድ፣ ቺሊ እና ስዊድን ከምድብ ወደ ሩብ ፍፃሜው ለመሻገር ይፎካከራሉ፡፡rnrnእስካሁን በተካሄዱ ሰባት ውድድሮች አሜሪካ ሶስት ጊዜ ዋንጫ ስታነሳ፣ ጀርመን ሁለት ጊዜ እንዲሁም ካናዳ እንዲሁም ጃፓን እና ኖርዌይ አንድ ጊዜ ባለድል ሆነዋል፡፡rnrnበ8ኛው የሴቶች ዓለም ዋንጫ 27 ዋና ዳኞች እና 48 ረዳት ዳኞች ይመራል፡፡ ከካፍ በኩል 3 ዋና እና 4 ረዳት አርቢትሮች ተመርጠዋል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ደግሞ አፍሪካን ከወከሉ አርቢትሮች አንዷ ነች፡፡rnrnበቪዲዮ የተጋዘ ዳኝነት /ቫር ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ውድድር ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጧል፡፡rnrnለአንድ ወር የሚዘልቀውን ይሄንን የዓለም ዋንጫ ውድድር ለመታደም አንድ ሚሊዬን ተመልካቾች ቲኬቶችን እንደቆረጡ በቢቢሲ ተጠቅሷል፡፡