Arts TVArts TV
← NewsSport

48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

Arts TV · ሜይ 7 2019

48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

ከ1963 ጀምሮ በየዓመቱ ሲካሄድ የነበረው ይህ ውድድር ዘንድሮ ለ48ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሚያዚያ 29- ግንቦት 4/2011 ዓ/ም በ36 ክለቦችና ተቋማት መካከል ሲደረግ በአጠቃላይ 1376 አትሌቶች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡ rnrnየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁሉንም የአትሌቲክስ የውድድር ተግባራት በመካተት የሚካሄድ ይሆናል፡፡  rnrnየውድድሩ ዓላማ በአገር ውስጥ የውድድር ዕድል መፍጠር ፤ በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች እንዲሁም ተቋማት መካከል የአትሌቲክስ ፉክክር መፍጠር፣ ለብሔራዊ ቡድን አትሌቶች ለመምረጥ እና ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሚኒማ ሊያሟሉ የሚችሉ አትሌቶችን በዕጩነት ለመምረጥ የሚል ነው፡፡rnrnየውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች፣ ከአንዴ በላይ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያስመዘግቡ እና በቡድን ውጤት ለሚያስመዝግቡ አትሌቶች አንዲሁም ክብረወሰን ለሚያሻሽሉ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት ይኖራል ተብሏል፡፡rnrnከ2.1 ሚሊየን ብር በላይ በጀት የተያዘለት ይህ ሻምፒዮና አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ ተገልጧል፡፡

More in Sport