የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ የሆኑት እንግሊዛዊው ስቴዋርት ሃል ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው የለቀቁ መሆኑን ትናንት ለስፖርት ማህበሩ በፃፉት ድብዳቤ አሳውቀዋል።rnrnየቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ትናንት ከሰዓት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አሰልጣኙ በራሳቸው ፈቃድ የለቀቁበትን ደብዳቤ ተመልክቶ ጥያቂያቸውን ተቀበሎታል፡፡ rnrnአሰልጣኙ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ ላደረገላቸው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡ rnrnስራ አመራር ቦርዱም፤ አሰልጣኙ በክለቡ ቆይታቸው ወቅት ላከናወኗዋቸው ተግባራት አመስግኖ ቀጣይ ጨዋታዎችን ምክትል አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ዋና አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ ሰይሟል ሲል የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ አስታውቋል፡፡rnrnበዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እስካሁን በተደረጉ የ24 ሳምንታት ጉዞ አስሩን በድል ሲወጣ፣ በስምንቱ አቻ ተለያይቶ በአምስት ጨዋታዎች ላይ ሸንፈት ገጥሞታል፡፡ rnrnሊጉ ሊጠናቀቅ የስድስት ሳምንታት እድሜ የቀሩት ሲሆን ጊዮርጊስ 39 ነጥቦችን ሰብስቦ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
ጊዮርጊስ እና አሰልጣኝ ስቴዋርት ሃል በይፋ ተለያይተዋል፡፡
Arts TV · ሜይ 15 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019