በሚቀጥለው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዓመት የሚሳተፍ ሶስተኛውን ክለብ ለመለየት ዛሬ አመሻሽ 11፡00 ሰዓት በግዙፉ ዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል፡፡rnrnተፋላሚዎቹ ደግሞ አስቶን ቪላ እና ደርቢ ካውንቲ ናቸው፤ በቼልሲ አብረው ስኬትን የተቋደሱት ጆን ቴሪ እና ፍራንክ ላምፓርድ ደግሞ በአሰልጣኝነት የተለያዩ ቡድኖችን ይዘው ተፋጥጠዋል፡፡rnrnየቪላ አሰልጣኝ ዲን ስሚዝ ምክትል ሆኖ እያገገለገለ የሚገኘው ቴሪ ሲሆን ላምፓርድ ደርቢን በዋና አሰልጣኝነት በተረከበበት ዓመት ወደ ሊጉ ሊያሻግረው ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡rnrnበደርሶ መልስ ጨዋታዎች አስቶን ቪላ ዌስት ብሮም አልቢዮንን እንዲሁም ደርቢ ካውንቲ የማርሴሎ ቤልሳውን ሊድስ ዩናይትድ በመጣል ነበር ለዚህ የፍፃሜ ጨዋታ መብቃት የቻሉት፡፡rnrnየጨዋታው አሸናፊ ከኖርዊች እና ሼፊልድ ዩናይትድ በመከተል፤ 170 ሚሊዬን ፓውንድ ጋር ሶስተኛው 2019/20 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ቡድን መሆኑን ያረጋግጣል፡፡rnrnበቻምፒዮንሽፑ የውድድር ዓመት ቪላ በፍራንክ ላምፓርድ ቡድን ላይ ሁለቱን ጨዋታ (በ3 ለ 0 እና 4 ለ 0) ድል በማድረግ የበላይነት አለው፡፡rnrn
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
የ170 ሚሊዬን ፓውንድ ዋጋ ያለው ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል፡፡
Arts TV · ሜይ 27 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019