Arts TVArts TV
← NewsSport

የኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት ይደረጋል፡፡

Arts TV · ሜይ 24 2019

የኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት ይደረጋል፡፡

117ኛው የስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ወይንም የስፔን ንጉስ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በነገው ዕለት ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡rnrnግጥሚያው በባርሴሎና እና ቫሌንሲያ መካከል ሲቪያ ውስጥ በሚገኘው በሪያል ቤትስ ቤኒቶ ቪያማሪን ስታዲየም ይደረጋል፡፡rnrnበአሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ የሚመራው የካታላኑ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው ተቀናቃኙን ሪያል ማድሪድ በደርሶ መልስ 4 ለ 1 ድል በማድረግ ለተከታታይ ስድስተኛ የፍፃሜ ጨዋታ ሲበቃ የተመሰረተበትን መቶኛ ዓመት እያከበረ የሚገኘው የማርሴሊኖው ቡድን ቫሌንሲያ ደግሞ ሪያል ቤቲስን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል፡፡   rnrnባርሳ 41ኛውን የፍፃሜ ጨዋታ የሚያደርግ ሲሆን ለአምስተኛ ተከታታይ ድሉ፤ በአጠቃላይ ደግሞ ለ31ኛ የንጉስ ዋንጫ ድሉ ይጫወታል፡፡ ቫሌንሲያ እስካሁን 7 ጊዜ ዋንጫውን ከፍ ያደረገ ሲሆን ለስምንተኛ ድሉ ይፋለማል፡፡rnrnቫሌንሲያ ዋንጫውን ለመጨረሻ ጊዜ ያነሳው በ2008 ቪንሴንቴ ካልዴሮን ላይ ሄታፌን 3 ለ 1 በማሸነፍ ነበር፡፡rnrnጨዋታው በአርቢትር አልቤርቶ ኡንዲያኖ ማዬንኮ ይመራል፡፡

More in Sport