የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ፤ የፍፃሜ ተፈላሚ ቡድኖች ትናንት በተካሄዱ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ተለይተው ታውቀዋል፡፡rnrnበዚህም ትናንት በሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ክለቦች ኢትዋል ዱ ሳህል እና ዛማሊክ መካከል በስታደ ኦሊምፒክ ደ ሱስ የተደረገው ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ፤ የግብፁ ቡድን ዛማሊክ በመጀመሪያው የአሌክሳንድሪያ ጨዋታ ወቅት በሜዳው 1 ለ 0 መርታቱን ተከትሎ በ1 ለ 0 ድምር ውጤት የቱኒዚያውን ቡድን በመጣል ለፍፃሜ ዋንጫ ማለፉን አረጋግጧል፡፡rnrnሌላኛው ግጥሚያ የሞሮኮው ቤርካኔ በሜዳው ስታዴ ሙኒሲፓል ዴ ቤርካኔ የቱኒዚያውን ሲ.ኤስ ሴፋክሲያንን አስተናግዶ 3 ለ 0 በመርታት ለፍፃሜ ጨዋታው መብቃት ችሏል፡፡ rnrnበመጀመሪያው ጨዋታ ሴፋክሲያን 2 ለ 0 ያሸነፈ ቢሆንም የሞሮኮው ቡድን ውጤቱን ቀልብሶ ለኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ፍፃሜ መድረሱን አረጋግጧል፡፡rnrnኮጆ ፎ ዶህ፣ ኦማር ኢናማሳይ እና ኢሱፉ ዳዮ ቤርካኔን ወደ ዋንጫው ጨዋታው ያሻገሩ የድል ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡rnrnቅዳሜ ዕለት የ2018/19 የቶታል ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ተጫዋቾች ሲለዩ፤ ኤስፔራንስ እና ዋይዳድ ካዛብላንካ እንደሚገናኙ ታውቋል፡፡rnrnየቱኒዚያው ኤስፔራንስ ደ ቱኒስ ወደ ኮንጎ ተጉዞ ከቲፒ ማዜምቤ ጋር ያለግብ ቢለያይም በመጀመሪያው ጨዋታ ቱኒስ ላይ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 ረትቶ አልፏል፡፡rnrnወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናው የሞሮኮው ዋይዳድ አትሌቲክ/ ዋይዳድ ካዛብላካ ደግሞ ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር በተመሳሳይ ያለግብ በአቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቅቋል፤ ዋይዳድ ሞሮኮ ላይ 2 ለ 1 በመርታቱ በዚሁ ድምር ውጤት ለፍፃሜው በቅቷል፡፡
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
የካፍ ኮንፌዴሬሽን የፍፃሜ ተፋላሚዎች ተለይተው ታውቀዋል
Arts TV · ሜይ 6 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019