rn
rnrnከ15 ዓመታት በፊት በ2004 የተጀመረው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በ16ኛ ዙር ውድደሩ ፍፃሜ ላይ ይገኛል፡፡ rnrnየ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታ ባለፈው ሳምንት የተከናወነ ሲሆን የመልስ ፍልሚያው ደግሞ በመጪው ዕሁድ ግብፅ አሌክሳንድሪያ ላይ በግብፁ ቡድን ዛማሊክ እና በሞሮኮው ሬኔይሳንስ ስፖርቲቭ ዴ ቤርካኔ መካከል ቦርጅ አል አረብ ስታዲየም ላይ ይደረጋል፡፡ rnrnሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ዕሁድ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ሞሮኮ ላይ አድርገው የነበረ ሲሆን ቤርካኔ ባለቀ የጭማሪ ሰዓት በቶጓዊው ተጫዋች ኮድጆ ፎ -ዶህ- ላባ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 ድል ማድረጉ ይታወቃል፡፡rnrnለ16 ዓመታት ያህል ያለባቸውን የአህጉራዊ ዋንጫ ድርቅ ዘንድሮ ለመግታት እየጣሩ የሚገኙት ዛማሊኮች፤ የመጀመሪያ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫቸውን ከፍ ለማድረግ፤ በሜዳቸው እና ደጋፊያቸው ፊት የሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ ላይ ቢያንስ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ግድ ይላቸዋል ፡፡ rnrnዛማሊክ ከዚህ ቀደም 5 የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ 3 የካፍ ሱፐር ካፕ ወይንም የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን በአፍሪካ መድረክ አሳክቷል፡፡ ነጭጭ ጀብደኞች በኮንፌሬሽን ዋንጫ ታሪክ ለፍፃሜ ሲበቁ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በውድድሩ ከዚህ በፊት ያላቸው ትልቅ ስኬት 2015 ያሳኩት የግማሽ ፍፃሜ ዙር ላይ መድረስ ነበር፡፡rnrn ዛማሊክ ለመጨረሻ ጊዜ የተቀዳጀው ዋንጫ የካፍ ሱፐር ካፕ ሲሆን በ2003 ካይሮ ላይ የሞሮኮውን ዋይዳድ ካዛብላንካ በመርታት ነው፡፡rnrnበቅፅል ስማቸው ዘ ኦሬንጅ ሲቲ ተብለው የሚጠሩት ቤርካኔዎች በ1938 ከተመሰረቱ በኋላ ለካፍ ውድድሮች ፍፃሜ ሲበቁ ይሄኛው የመጀመሪያቸው ነው፡፡ rnrnብርቱካናማዎቹ አዲስ ታሪክ ለማፃፍ ደግሞ የሜዳ ላይ አድቫንቴጅ ይዘው የመልስ ግጥሚያቸውን አሌክሳንድሪያ ላይ በሚገኘው 86 ሺ ተመልካች በሚይዘው የቦርጅ አል አረብ ስታዲየም የ90 ደቂቃ ብቻ ጊዜ ይቀራቸዋል፡፡rnrnይሄንን የፍፃሜ ግጥሚያ ኢትዮጵያዊው አርቢትር ባምላክ ተሰማ ወየሳ ይመራል፡፡ ረዳቶቻቸው ደግሞ ዛካሊ ሲዎሊ ከደቡብ አፍሪካ እና አልሃጂ ማሊክ ሳምባ ከሴኔጋል እንዲሁም አራተኛ ዳኛው አል- ሳዴቅ አል- ሳልሚይ ከቱኒዚያ ናቸው፡፡rnrnየኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊው ቡድን የ1.25 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሲሸለም፤ ተሸናፊው የ625 ሺ ዶላር ያገኛል፡፡rnrn
rn





