የ23ኛ ሳምንት የሊጉ መርሀግብር ግጥሚያዎች ዛሬ ሲጀመር በገዛህኝ ከተማ የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ ቡና ወደ ሽረ አቅንቶ ከስሑል ሽረ ጋር ይጫወታል፡፡rnነገ አንዲሁ ሌላ ጨዋታ ሲከናወን ወራጅ ቀጠና የሚገኘው ደደቢት ወደ ሶዶ አምርቶ ወላይታ ድቻን ይገጥማል፡፡rnቀሪዎቹ የሳምንቱ ፍልሚያዎች ዕሁድ ሲደረጉ፤ አንድ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲሁም ሌሎቹ በክልል ስታዲየም ይከናወናሉ፡፡rnቅዱስ ጊዮጊስ በሜዳው በመጣበት ዓመት ከሊጉ ላለመሰናበት እየጣረ የሚገኘውን ደቡብ ፖሊስ 10፡00 ሰዓት ሲል ያስተናግዳል፡፡rnክልል የሚደረጉት ጨዋታዎች በተመሳሳይ 9፡00 ሰዓት ሲካሄዱ፤ በሳምንቱ መረሀግብር ከሚከናወኑ ጨዋታዎች ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ጨዋታ ሃዋሳ ላይ በሲዳማ ቡና እና በሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ መካከል ይከናወናል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ካላቸው የነጥብ ልዩነት እና ወቅታዊ አቋም አንፃር ጨዋታውን በተሻለ ተጠባቂ ያደርገዋል፡፡rnሌላኛው ጥሩ ጨዋታ ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቀው ግጥሚያ ደግሞ ጎንደር ላይ ሲከናወን የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድን በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም በዩሃንስ ሳሕሌ የሚመራውን የትግራዩን ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ይገጥማል፡፡rnየአሰልጣኝ ለውጥ ካደረገ በኋላ ወደ ውጤት የተመለሰ የሚመስለው መከላካያ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማን ይጎበኛል ፤ የአምናው ሻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር ደግሞ በሜዳው ከሀዋሳ ከተማ ጋር ይጫወታል፡፡rnየጳውሎስ ጌታቸው ቡድን ባህር ዳር ከነማ በከተማው ግዙፍ ስታዲየም ከምስራቁ ድሬዳዋ ጋር ይፋለማል፡፡rnየሊጉን የደረጃ ሰንጠራዥ መቐለ በ48 ነጥቦች ሲመራ ፋሲል በ43 ይከተላል፡፡rnደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ እና በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይካሄዳሉ
Arts TV · ሜይ 10 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019

