ተጠባቂው የሸገር ደርቢ በዚህ ሳምንት መርሀግብር የሚከናወን ሲሆን በዕለተ ሰንበት 10፡00 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል ይደረጋል፡፡rnrnየበርካታ ደጋፊዎች ባለቤቶች ሁለቱ የአዲስ አበባ ክለቦች የዘንድሮው የሊጉ ውድድር የልብ ደጋፊዎቻቸውን ጭምር ያላስደሰተ ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡rnrnበመጀመሪያው ዙር ያለግብ በአቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፤ አሁን በሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥ ፈረሰኞቹ በ37 ነጥብ እና 13 ንፁህ ጎሎች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ፤ ቡናማዎቹ በ32 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ rnrnቅዳሜ ዕለት ሶስት ግጥሚያዎች ሲከናወኑ፤ ሁለቱ በክልል ስታዲየሞች ላይ በተመሳሳይ 9፡00 ይደረጋሉ፡፡ rnrnየጎንደሩ ፋሲል ከነማ ወደ ትግራይ ክልል በመጓዝ መቐለ ላይ በግዙፉ ስታዲየም የወራጅ ቀጠና ግርጌ ላይ የሚገኘውን ደደቢት የሚገጥም ይሆናል፡፡ rnrnሌላኛው ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ቡድን ደቡብ ፖሊስ ሀዋሳ ላይ አዳማ ከተማን ያስተናግዳል፡፡rnrnአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው (ማንጎ)ን ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ያደረገው ባህር ዳር ከነማ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ከመከላከያ ጋር ይጫወታል፡፡ የጣና ሞገዶቹ ከ20ኛ ሳምንት የሊጉ መርሀግብር እዚሁ ስታዲየም በኢትዮያ ቡና 5 ለ 0 መረታታቸው ይታወሳል፡፡ rnrnእሁድና ሰኞ የ22ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ በዕለተ ሰንበት ከሸገር ደርቢ በተጨማሪ ሶስት ግጥሚያዎች በክልል ስታዲየሞች እንዲሁም ሰኞ አንድ የሳምንቱ የማሳረጊያ ግጥሚያ በተመሳሳይ 9፡00 ሰዓት ይደረጋሉ፡rnrnየደቡቡ ክለብ ወላይታ ድቻ ወደ ምስራቅ አቅንቶ፤ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ይፋለማል፡፡ rnrnየሊጉ አናት ላይ የተቀመጠው መቐለ 70 እንደርታ በትግራይ ስታዲየም ከስሑል ሽረ ጋር ትልቅ ትንቅንቅ ያለበትን የትግራይ ደርቢ ጨዋታ ያደርጋል፡፡ መቐለ በሊጉ መሪነት ለመግፋት፣ ሽረ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት የሚደረግ ግጥሚያ መሆኑ ጨዋታው ይጠበቃል፡፡rnrnሀዋሳ ከተማ በደቡብ ደርቢ ከሲዳማ ቡና ጋር ጥሩ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡ ሰኞ ጅማ አባ ጅፋር በትግራይ ስታዲየም ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ይጎበኛል፡፡rnrnበኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ21 ሳምንታት ጉዞ መቐለ 70 እንደርታ በ45 ነጥቦች ቀዳሚ ነው፤ ፋሲል ከነማ በአምስት ነጥብ አንሶ 40 ነጥብ ሰብስቦ 2ኛ ደረጃን ይዟል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሲዳማ ቡና እና ጅማ አባ ጅፋር በተመሳሳይ 37 ነጥብ ባለቸው ንፁህ የግብ ክፍያ ከ3- 4 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪዎቹ የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይከናወናሉ
Arts TV · ሜይ 3 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019