<strong>በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ አንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ከክልሉ የባህል እና ስፖርት እንዲሁም የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንትን በሀዋሳ በመገኘት የሲዳማ እና የወላይታ ዲቻ ክለቦች በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ጨዋታዎቻቸውን በገለልተኛ ሜዳ እያደረጉ መሆኑ እንዲሁም ከግዜ ወደ ጊዜ ይህ ችግር ወደ ሌሎች ክለቦችም እየተዛመተ መሆኑ በ21ኛ ሳምንት ጨዋታ ደቡብ ፖሊስ ከወላይታ ዲቻ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በደጋፊዎች መካልከል በነበረው ግጭት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በተመለከተ መፍትሄ ለማፈላለግ እና የሁለቱን ህዝቦች ለማቀራረብ በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ነጥቦች ላይ የጋራ ምክክር ተካሂዷል። </strong>rnrn<strong>ውይይቱም ውጤታማ እና በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ ትልልቅ የውይይት መድረኮች የክለቦቹ ደጋፊ ማህበራት እና የየክለቦቹ አመራሮች ብሎም የጸጥታ አካላት በተገኙበት በወላይታ እና በሃዋሳ ውይይት በማድረግ ችግሩን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅረፍ ቃል ገብተዋል። </strong>rnrn<strong>በቀጣይ መሰል ውይይቶችን ክልሉ አጠናክሮ በመቀጠል የህዝብ ለህዝብ ቅርርቡን ለማጠናከር እንደሚሰራ እና እግር ኳስ የተራራቀውን ህዝብ ማገናኛ ድልድይ እንጂ ማራራቂያ ሊሆን እንደማይገባ ተገልጿል።</strong>rnrn<strong>የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም ጨዋታቸውን በገለልተኛ ሜዳ ያካሂዱ የነበሩትን የትግራይ እና የአማራ ክልል ክለቦች እንዲሁም የክልል ሀላፊዎች እና የደጋፊ ማህበራት የፌዴሬሽን ጥያቄን በመቀበል በሜዳቸው ጨዋታቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።</strong>
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ከደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት አደረጉ::
Arts TV · ሜይ 2 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019

