Arts TVArts TV
← NewsSport

የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ማሩዋን ቻማክ ጫማ ሰቅሏል፡፡

Arts TV · ሜይ 27 2019

የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ማሩዋን ቻማክ ጫማ ሰቅሏል፡፡

በተለያዩ ክለቦች የተጫወተው ሞሮኳዊው ኢንተርናሽናል ማሩዋን ቻማክ ላለፉት rnrnሁለት ዓመት ከግማሽ ሳይጫወት ከቆየ በኋላ በ35 ዓመቱ በይፋ እግር ኳስ  መጫወት ማቆሙን አስታውቋል፡፡rnrnየቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች በዌስት ሃም ዩናይትድ፣ ክሪስታል ፓላስ፣ ካርዲፍ ሲቲ እና የፈረንሳዩ ቦርዶ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡rnrnተጫዋቹ በ2016 የዌልሱን ካርዲፍ ከተሰናበተ በኋላ ያለምንም ክለብ ቆይታ አድርጓል፡፡rnrnቻማክ ለቤን ስፖርትስ እንዳለው በእውነት ዛሬ ከእግር ኳስ መገለሌን አስታውቃለሁ ሲል ገልጧል፡፡rnrnበፈረንሳይ የተወለደው ቻማክ ስምንት ዓመታትን በቦርዶ በማሳለፍ፤ በ230 የሊጉ ጨዋታዎች ላይ 56 ጎሎችን በማስቆጠር፤ አንድ የሊግ አንድ እና የፈረንሳይ ሊግ ዋጫዎችን ማሳካት ችሏል፡፡rnrnበ2010 ወደ አርሰናል መጥቶ በሶስት የውድድር ዓመት ቆይታው፤ በ40 የፕሪምየር ሊግ ግጥሚያዎች ላይ ተሰልፎ ስምንት ጎሎችን ብቻ አስቆጥሯል፡፡rnrnቻማክ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ለፈረንሳይ ከ19 ዓመት በታች ቢሰለፍም፤ ዋናውን የብሄራዊ ቡድን አገልግሎት ግን ለሞሮኮ ከ2003 ጀምሮ ሰጥቷል፡፡ ለሀገሩም በ68 ግጥሚያዎች 18 ግቦችን ማበርከት ችሏል፡፡

More in Sport