የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከጋምቢያ አቻቸው ጋር ላለባቸው የወዳጅነት ጨዋታ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጓን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድረ ገፅ ይፋ አድርጓል።rnrnበጋምቢያ ባካው ከተማ ላይ ሰኔ 8 እና 11 ሉሲዎቹ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ለዚህም እንዲረዳት አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለተጫዋቾች ጥሪ አድርጋለች።rnrnከግብ ጠባቂዎችrnrnየጥረት ኮርፖሬቷ ታሪኳ በርገና፤ የሀዋሳ ከተማው አባይነሽ ኤርቄሎ፤ የመከላከያዋ ማርታ በቀለ ጥሪ ደርሷቸዋል፡፡ rnrnበተከላካይ መስመር rnrnመስከረም ኮንካ፣ ናርዶስ ጌትነት፣ እጸገነት ብዙነህ፣ ነጻነት ጸጋዬ ከአዳማ ከተማ፤ ገነሜ ወርቁ እና ብዙአየሁ ታደሰ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ መሰሉ አበራ ከ መከላከያ እና የሐዋሳ ከተማዋ ቅድስት ዘለቀ ተመርጠዋል፡፡rnrnከአማካኝ ተጫዋቾች ደግሞ ህይወት ደንጊሶ እና ብርቱካን ገ/ክርስቶስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ከመከላከያ እመቤት አዲሱ እና አረጋሽ ካልሳ፤ አለምነሽ ገረመው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፤ ሰናይት ቦጋለ ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ይመችሽ ዘውዴ ከድሬዳዋ ከተማ ተካትተዋል፡፡rnrnበአጥቂ ስፍራ rnrnሎዛ አበራ፣ ገነት ሀይሉ፣ ሴናፍ ዋቁማ እና ሰርክአዲስ ጉታ ከአዳማ ከተማ፤ መዲና ጀማል እና ሔለን እሸቱ ከመከላከያ እና ምርቃት ፈለቀ ከሀዋሳ ከተማ ጥሪ ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡rnrnጥሪ የደረሳቸው እነዚህ ተጫዋቾች በነገው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አደረገች::
Arts TV · ጁን 7 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019