የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የመልስ ግጥሚያ ትናንት ምሽት ግብፅ ላይ ተካሂዷል፡፡rnrn
rnrnየፍፃሜው ጨዋታ ደግሞ ግብፁ ኤል ዛማሊክ እና የሌላኛዋ ሰሜን አፍሪካዊት ሀገር ሞሮኮ ተወካይ ሬነሳንስ ስፖርቲቭ ዴ ቤርካኔ መካከል ዛማሊክ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት 5 ለ 3 በመርታት በታኩ የመጀመሪያውን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሳክቷል፡፡rnrnሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ሞሮኮ ላይ የመጀመሪያ ግጥሚያቸውን አድርገው፤ ቤርካኔ ባለቀ ሰዓት ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 መርታት ቢችሉም፤ በትናንት ምሽቱ የቦርጅ አል አረብ ስታዲየም ፍልሚያ ዛማሊክ በሜዳው በተመሳሳይ 1 ለ 0 ውጤት ድል አድርጓል፡፡ ማሃሙድ አላ ደግሞ ለግብፁ ቡድን የድሏን ጎል ከመረብ አገናኝቷል፡፡rnrnሁሉቱ ቡድኖች በደርሶ መልሱ ጨዋታ 1 ለ 1 አቻ መለያየታቸውን ተከትሎ፤ በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት የግብፁ ዛማሊክ 5 ለ 3 በማሸነፍ ለ16 ዓመታት የናፈቀውን አህጉራዊ ዋንጫ ከ2003 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሟል፡፡rnrnለአህጉራዊ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍፃሜ የደረሰው ቤርካኔ የመጀመሪያ ውጤቱን ባለማስጠበቁ ተሸንፏል፡፡ rnrnየፍፃሜ ጨዋታውን ኢትዮጵያዊው አርቢትር በአምላክ ተሰማ መርቶታል፡፡rnrnዛማሊክ የውድድሩ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ የዋንጫ እና የ1.25 ሚሊዬን የአሜሪካን ዶላር ሽልማት ሲያገኝ፤ ቤርካ የ625 ሺ ዶላር አግኝቷል፡፡