Arts TVArts TV
← NewsLegal

በካሜሮን የታገቱ ተማሪዎችን ፍለጋ ቀጥሏል

Arts TV · ኖቬም 7 2018

በካሜሮን የታገቱ ተማሪዎችን ፍለጋ ቀጥሏልrnrnአርትስ 28/02/2011rnrn rnrnየካሜሮን ባለ ስልጣናት ባለፈው ሰኞ በታጠቁ ሀይሎች ታግተው የተወሰዱ 79 ተማሪዎች እና 3 የትምህርት ቤቱ የስራ ባልደረቦችን ፈልጎ በህይወት የማገኘቱ ስራ በአስቸኳይ እንዲከናወን ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡rnrnየሀገሪቱ ሰሜን ምእራብ አስተዳዳሪ ዲበን ቻፎ እንዳሉት ከተማሪወቹ በተጨማሪ የትምህርረት ቤቱ ሀላፊ፣ ሾፌርና መምህር በነዚህ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው የካሜሮን ወታደራዊ ቃል አቀባይ በሀገሪቱ የእንገንጠል ጥያቄ የሚያነሱ ሀይሎች ናቸው ድርጊቱን የፈፀሙት በማለት ሀላፊነቱን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡rnrnየሀይማኖት አባቶች በበኩላቸው ድርጊቱን አውግዘው ህጻናቱና የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡rnrnተማሪወቹ የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ስም እንዲናገሩ በአጋቾቻቸው ሲጠየቁ  በማህበራዊ ድረ ገፅ በተለቀቀ የቪዲዮ ምስል ታይተዋል ነው የተባለው፡፡

More in Legal