ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም አዋጅ አፀደቀች፡፡rnrnየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ ስብሰባው የጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ አፅድቋል፡፡rnrnየረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ መስፍን ቸርነት የአገርና የህዝብን ፀጥታ እና ሰላም ለማስጠበቅ ያለመ ነው ብለዋል፡፡rnrnግለሰቦች የታጠቋቸውን መሳሪዎች የሕብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ተግባር ላይ እንዲያውሉ እንዲሁም ህገ-ወጥ የጦር መሳሪዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር እንደሚያስችልም አብራርተዋል፡፡rnrnበውይይቱ ወቅት የጦር መሳሪያ ፈቃድ የሚሰጣቸው አካላት መስፈርት በጣም ቀላል በመሆኑ ማንኛውም አካል ዝም ብሎ መሳሪያ እንዲታጠቅ በር አይከፍትም ወይ የሚል ጥያቄ ተነስቶም ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡rnrnመረጃው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡






