Arts TVArts TV
← NewsSport

ስፔናዊው አጥቂ ፈርናንዶ ቶሬስ ከእግር ኳስ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

Arts TV · ጁን 21 2019

ስፔናዊው አጥቂ ፈርናንዶ ቶሬስ ከእግር ኳስ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡
ስፔናዊው አጥቂ ፈርናንዶ ቶሬስ ከእግር ኳስ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡rnrnየቀድሞው የአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ሊቨርፑል እና ቼልሲ ተወዳጅ ተጨዋች ፈርናንዶ ቶሬስ በ35 ዓመቱ እግር ኳስ መጫወት ማቆሙን ይፋ አድርጓል፡፡rnrnrnrnቶሬስ የ18 ዓመት የፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቱን መግታቱን እና የጃፓኑን J1 ሊግ ሳጋን ቶሱ ክለብ ደግሞ የመጨረሻው ሆኗል፡፡ rnrnለሀገሩ ስፔን ብሔራዊ ቡድን በስድስት ትልልቅ ውድድሮች ላይ በማገልገል፤ 110 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፤ 38 ጎሎችንም አበረክቷል፡፡ የብሔራዊ ቡድኑም ሶስተኛው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው፡፡ የዩሮ 2008 እና 2012 እንዲሁም የ2010 የዓለም ዋንጫዎችንም ከሀገሩ ልጆች ኮከቦች ጋር በመሆን አሳክቷል፡፡rnrnrnrn‹‹ ከ18 አመርቂ ዓመታት በኋላ የእግር ኳስ ህይወቴ ተጠናቅቋል›› ሲል ቶሬስ በትዊተር ገፁ አስፍሯል፡፡rnrnተጫዋቹ እግር ኳስን በአትሌቲኮ ዴ ማድሪድ መጫወት የጀመረ ሲሆን በ2007 በ20 ሚሊዬን ፓውንድ ሂሳብ ወደ እንግሊዙ ሊቨርፑል በማምራት በቀዩ ማሊያ 142 ጨዋታዎች ላይ 81 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡ ያለውን ልዩ ክህሎትም በትልቁ በዚሁ በመርሲ ሳይዱ ክለብ ማሳየት ችሏል፡፡rnrnrnrnበ2011 ደግሞ በጊዜው የብሪታኒያ የተጫዋቾች የዝውውር ክብረወሰን በሆነ የ50 ሚሊዬን ፓውንድ ዋጋ ወደ ቼልሲ በማቅናት፤ ከሰማያዊዎቹ ጋር እስከ 2014 ድረስ በመቆየት በ172 ጨዋታዎች ተሰልፎ 45 ጎሎችን በማበርከት በ2012 የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ፣ በ2013 የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ፣ የኤፍ ኤ ዋንጫ ድል አሳክቷል    ከዚያም በጣልያኑ ኤስ ሚላን የአራት ወራት የውስት ውል ቆይታ ካደረገ በኋላ፤ በ2014 ወደ ቀድሞ ክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ በመመለስ በ2017/18 ዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ፤ በ2015/16 ቻምፒዮንስ ሊግ ከቡድኑ ጋር ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡rnrnrnrnከአትሌቲ ጋር ዩሮፓ ሊግ ካሳካ በኋላ ወደ ጃፓን ሊግ አምርቷል፡፡ በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቱ በ756 ጨዋታዎች 260 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡rnrnrnrnበእግር ኳስ ህይወቱ በግል ከወጣትነቱ ጀምሮ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ኮከብ እየተሰኜ ያደገ ሲሆን በ2007/08 እና በ2008/09 በተከታታይ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ምርጥ ቡድን ስብስብ ውስጥ ተካትቷል፤ በሊጉ የወሩ ኮከብ ተጫዋች፤ የአውሮፓ ምርጥ ቡድን ስብስብ ውስጥ መካተት፣ የፊፋ ምርጥ ቡድን እና ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ በመካተት ክብር አግኝቷል፡፡  rnrn 

More in Sport